Skip to content

Latest commit

 

History

History
454 lines (229 loc) · 55.6 KB

amharic.md

File metadata and controls

454 lines (229 loc) · 55.6 KB

BBC News አማርኛ

የትግራይ ክልል ቀውስ፡ ከፕሪቶሪያ ወዲህ መቼ ምን ተከሰተ?

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 4:47:53

ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን አውዳሚ ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ትግራይ ክልል ዳግም ወደ ቀውስ እያመራ ነው። አሁን የተከሰተው ችግር ለሁለት በተከፈሉት በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረ ነው። የአሁኑ ቀውስ ከመፈጠሩ በፊት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት የታለፈበት መንገድ ምን ይመስላል?

በበረራ ወቅት ተሳፋሪ ቢሞት ምን ይደረጋል?

እሑድ 16 ማርች 2025 ጥዋት 4:30:16

ሁሉ መልካም ነው ብለው በአውሮፕላን ተሳፍረው ከሚያቀኑ መንገደኞች መካከል አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሕይወታቸው በበረራ ወቅት ቢያልፍ ምን ይደረጋል?

በቤንሻንጉል ክልል የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ያነሱት የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ተነሳ

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 9:35:23

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ተሰማ ግጭትን የሚቀሰቅሱ፣የክልሉን እና የምክር ቤቱን ክብር የሚነኩ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው ያለ መከሰስ መብታቸው መነሳቱ ተገልጿል።

ትግራይ፡ "ማንም ሌላ ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ የለውም"

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 7:04:39

በትግራይ ክልል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም.የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ አብቅቷል።

አንጎላ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ፖለቲከኞችን አላስገባም አለች

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 5:55:27

አንጎላ የአገሪቱ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ የተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮችን ወደ አገሯ እንዳይገቡ መከልከሏ ቁጣ አስነሳ።

አሜሪካ የደቡብ አፍሪካውን አምባሳደር ልታባርር ነው

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 6:40:28

አሜሪካ በመዲናዋ ዋሽንግተን ተቀማጩን የደቡብ አፍሪካውን አምባሳደር ልታባርር መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታወቀች።

ሱዳን ተፋላሚዬን ትደግፋለች በሚል ከኬንያ የሚገቡ ምርቶችን በሙሉ አገደች

ቅዳሜ 15 ማርች 2025 ጥዋት 4:55:44

ሱዳን ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት ከሠራዊቱ ጋር እየተዋጋ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ)ን በናይሮቢ ማስተናገዷን ተከትሎ ከኬንያ የሚገቡ ምርቶችን በሙሉ አገደች።

የኢትዮጵያ መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው ሲል ከሰሰ

ዓርብ 14 ማርች 2025 ከሰዓት 5:28:47

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ የአገሪቱ ተቀናቃኝ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እና ትብብር አለው በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰሰ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ይህንን ያሉት አርብ አዲስ አበባ ውስጥ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በክልሉ ስላለው ሁኔታ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው።

"ለምንድን ነው ከትግራይ የምሸሸው? . . . እመለሳለሁ" አቶ ጌታቸው ረዳ

ሐሙስ 13 ማርች 2025 ጥዋት 7:50:18

በትግራይ በህወሓት አመራሮች ያለው አለመግባባት ተባብሶ ወደ ኃይል እርምጃ እያመራ ይገኛል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ክስተት "እብደት" በማለት ድርጊቱ ክልሉን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊወስደው ይችላል ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው። ባለፉት ቀናት ከተከሰቱን ሁኔታዎች ጋር አቶ ጌታቸው የት እንዳሉ፣ የፌደራል መንግሥት ድጋፍን ስለመጠየቃቸው እና ስለሌሎችም ጉዳዮች ለቢቢሲ ኒውስ ምላሽ ሰጥተዋል።

መቀለ አቅራቢያ በምትገኘው አዲጉዶም ከተማ  የተከሰተው ምንድን ነው?

ረቡዕ 12 ማርች 2025 ከሰዓት 3:30:18

ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ከመቀለ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው አዲጉዶም ከተማ፣ በደብረፅዮን ገብረሚካኤልን (ዶ/ር) በሚመራው የህወሓት ክንፍ ይደግፋሉ የተባሉ የትግራይ ኃይል አባላት በንፁኅን ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍተው አራት ሰዎች ማቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና ተጐጂዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ፑቲን ከዩክሬን ጋር ለሚደረግ የተኩስ አቁም ከበድ ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጡ

ዓርብ 14 ማርች 2025 ጥዋት 5:12:45

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር እንዲደረስ የታቀደውን የተኩስ አቁም ሃሳብ እንደሚስማሙበት ቢገልጹም፤ በርካታ "ጥያቄዎች" የጫሩ ከባድ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል።

የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ 'ከአገራቸው አታልለው ያመጧትን" ወጣት በዩኬ በባርነት በማሰራት ጥፋተኛ ተባሉ

ዓርብ 14 ማርች 2025 ጥዋት 10:56:31

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲሁም የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከአገራቸው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም "አታልለው ያመጧትን" ወጣት በመኖሪያ ቤታቸው በባርነት እንድትሰራ በማስገደድ ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ።

አቶ ጌታቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ማህተም ከነጠቀ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ ጠየቁ

ሐሙስ 13 ማርች 2025 ጥዋት 11:33:16

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ "ለራሱ የግል እና የቡድን ጥቅም ሲባል የሕዝብን ሠላም፣ የፕሪቶሪያን ስምምነት፣ የአገሪቱን መረጋጋት እንደ መያዣ ከተጠቀመ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ።ክፍፍል ውስጥ በገቡት የህወሓት ክንፎች ምክንያት ቀውስ ውስጥ የገባውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚመሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን ያሉት ሐሙስ መጋቢት 4፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

"በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ

ማክሰኞ 11 ማርች 2025 ጥዋት 5:15:02

ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል "በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" በማለት አስጠነቀቁ።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በግልጽ የሚታይ መቃቃር አለ። የእኔ ስጋት ይህ ከቃላት አልፎ ወደ ጦርነት እንዳያድግ ነው" ብለዋል።

ኢንሱሊን መላመድ ምንድን ነው? በፆም ወቅትስ እክል ይፈጥራል?

ዓርብ 14 ማርች 2025 ጥዋት 4:00:54

በጡንቻ፣ በስብ እና በጉበት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ለኢንሱሊን መስጠት ያለባቸውን ምላሽ ሲያስተጓጉሉ ኢንሱሊን መላመድ ተፈጥሯል ማለት ነው። ከደም ውስጥ ጉሉኮስ ወስዶ ማከማቸት እንዲሳናቸው ያደርጋል።

በርካታ የሰላም ስምምነቶች በሳዑዲ አረቢያ እና በኳታር የሚካሄዱት ለምንድን ነው?

ማክሰኞ 11 ማርች 2025 ጥዋት 4:21:50

ዛሬ ማክሰኞ የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለስልጣናት በሳዑዲ አረቢያ ከሩሲያ ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ።አገሪቱ ለዚህ የሰላም ውይይት የተመረጠችው መሪዋ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባላቸው ጠንካራ ግንኙነት የተነሳ ነው። ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ዓለም አቀፍ የሰላም አደራዳሪ እንዲሆኑ የተመረጡት ለምንድን ነው? በመካከላቸው ቁርሾስ ፈጥሮ ይሆን?

"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ

ዓርብ 7 ማርች 2025 ጥዋት 3:50:04

ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?

በርካታ አፈታሪኮች፣ ምልኪዎች እና ትንግርቶች ያሏት ሙሉ ጨረቃ

ረቡዕ 12 ማርች 2025 ጥዋት 4:17:41

ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት አስገራሚ ክስተቶች እንደሚፈጠሩ ለዘመናት በርካታ አፈ ታሪኮች ተነግረዋል። አማልክት የሚገለጡበት፣ ሰዎች ወደ ተኩላነት መቀየር፣ አዕምሯቸውን የሚስቱበት ሌላም ሌላም . . . ሙሉ ጨረቃ ስትታይ የሚካሄዱ ፌስቲቫሎች፣ ምልኪዎች ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ባለው ዘመን ቀጥለዋል። እነዚህ ሁሉ ምን ያህል እውነትነት አላቸው?

ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሴቶች የሆኑባቸው አገራት፤ ሴቶች እና ፖለቲካ

ቅዳሜ 8 ማርች 2025 ጥዋት 4:18:52

አንዳንድ አገራት የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጎልበት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ ከመሪነት ቦታ ላይ ለመድረስ ችለዋል። አሜሪካ እና ጃፓንን የመሳሰሉ ያደጉ እና በዴሞክራሲ የዳበረ ልምድ ያላቸው አገራት ግን እስካሁን አንድም ሴት ፖለቲከኛ ከመሪነት መንበር ላይ ለመውጣት አልቻለችም። በተቃራኒው ባርቤዶስን የመሳሰሉ ጥቂት አገራት ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት ለማግኘት ታድለዋል።

ከቤት ሠራተኝነት እስከ ሆቴል ባለቤትነት - የአዲሲኒያ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት

ቅዳሜ 8 ማርች 2025 ጥዋት 4:17:42

አዲስ ገብረማርያም የልጅነት ሕይወቷ፣ እጅግ ከባድ እና ውስብስብ ነበር። በኢኮኖሚ ችግር፣ በስደት እና በጦርነት ምክንያት በፈተና የተሞላ ሕይወት ማሳለፏን ታስታውሳለች። ቤተሰቦቿ መሠረታዊ ነገሮች ለሟሟላት ይቸገሩ ነበር። የበኩር ልጅ በመሆኗ ደግሞ ሁሉም ዓይነት ኃላፊነቶች ጫንቃዋ ላይ የወደቀው በእርሷ ላይ ነው።

ባይተዋር ከተማ፡ "ፒያሳ፣ ካዛንቺስ . . . ሰፈሬ አልመስል አሉኝ"

እሑድ 9 ማርች 2025 ጥዋት 4:54:08

ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳሰዋል።

ራስን ማጥፋት ወንጀል ወይስ የጤና እክል? የኢትዮጵያ ሕግ ራስን ስለማጥፋት ምን ይላል?

ማክሰኞ 25 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:18:23

የተለያዩ የዓለም አገራት ሕይወታቸውን ለማጥፋት ሙከራ የሚያደርጉ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይመለከቷቸዋል። አንዳንዶች ድርጊቱን ወንጀል በማድረግ ሙከራ ያደረጉትን ሰዎች በእስር እና በተለያዩ መንገዶች ይቀጣሉ። ሌሎች ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል በመሆኑ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋሉ። እራስን ለማጥፋት መሞከር ወንጀል ወይስ . . . ? የኢትዮጵያ ሕግስ ይህንን ጉዳይ እንዴት ይመለከተዋል?

በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒት

ረቡዕ 12 ማርች 2025 ጥዋት 4:12:46

በዩናይትድ ኪንግደም ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ችግር የገጠማቸው ሴቶች የተሰጣቸው መድኃኒት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተነገራቸው ለቢቢሲ ገለጹ። ሕክምና ከወሰዱ መካከል 20 ሴቶች ለቢቢሲ እንደገለጹት የተሰጣቸው መድኃኒት "አሉታዊ ወሲባዊ ባህሪ" እንዲያዳብሩ የሚያደርግ መሆኑ አልተነገራቸውም።

የእንጀራ ልጇን ለ20 ዓመታት አግታለች የተባለችው አሜሪካዊት በቁጥጥር ስር ዋለች

ዓርብ 14 ማርች 2025 ጥዋት 8:25:59

ለ20 ዓመታት ያህል በእንጀራ እናቱ ታግቶ የነበረው አሜሪካዊ የተያዘበት ክፍል ላይ እሳት በመለኮስ ማምለጡን ባለስልጣናቱ ተናገሩ። ቃጠሎውን ተከትሎ የመጡ ባለስልጣናት በጠባብ ክፍል ታግቶ ነበረውን የ32 ዓመቱ ግለሰብ መታደጋቸውም ተነግሯል።

ሃዲድ ላይ ተኝቶ ባቡር በላዩ ላይ ከሄደበት በኋላ በተአምራዊ ሁኔታ የተረፈው ግለሰብ

ሰኞ 10 ማርች 2025 ጥዋት 6:44:14

በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ሰክሮ በከተማዋ ውስጥ በሚያቋርጥ የባቡር ሃዲድ ላይ ተኝቶ ሳለ ባቡሩ በላዩ ላይ ሄዶበታል። ነገር ግን ግለሰቡ ከባድ ጉዳት ሳይደርስበት ከአሰቃቂው አደጋ ለመትረፍ ችሏል። የአካባቢው አስተዳደር ግለሰቡ በተአምራዊ ሁኔታ የተረፈበትን አሰቃቂ አደጋ የሚያሳይ ቪዲዮን አጋርቷል።

"'ወንድ ነሽ ተብዬ' ከሴቶች እግር ኳስ ተገለልኩ" መሳይ ተመስገን

ቅዳሜ 1 ማርች 2025 ጥዋት 4:42:22

መሳይ ተመስገን በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ውስጥ ድንቅ ብቃት አለቸው ከሚባሉት መካከል ትጠቀሳለች። እግር ኳስን በሰፈር ውስጥ የጀመረችው መሳይ እስከ ኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተጫውታለች። የት ትደርሳለች የተባለቸው ተጫዋች “ጾታዋ ልክ” አይደለም በሚል ከእግር ኳስ ጋር ተለያይታለች።

በምሥራቅ እስያ በርካቶች ሃይማኖታቸውን መተው ወይም መቀየርን ለምን መረጡ?

እሑድ 23 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:39:27

በምሥራቅ እስያ ውስጥ በሚገኙ አገራት የሚኖሩ በርካታ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው በመውረስ ሲከተሉ የቆዩትን ሃይማኖት እርግፍ አድርገው እየተዉ መሆናቸውን ጥናት አመለከተ። የተወሰኑት ፊታቸውን ወደ ሌላ እምነት ሲያዞሩ፤ አብዛኞቹ ግን ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር ቁርኝት እንዳይኖራቸው የሚፍልጉ ናቸው። ይህ መጠንም ከተቀረው ዓለም ይልቅ በምሥራቅ እስያ ከፍተኛ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው?

"ቲክቶክ በአፍሪካ ሕጻናትን በሚያካትቱ ወሲባዊ ቀጥታ ሥርጭቶች ትርፍ እያገኘ ነው"

ማክሰኞ 4 ማርች 2025 ጥዋት 4:02:05

ቲክቶክ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሚከናወኑ የወሲባዊ ይዘቶች የቀጥታ ሥርጭቶች ትርፍ እያገኘ መሆኑን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምዕራባውያንን ያሳሰበው የፑቲን ምሥጢራዊ የጥቃት መሳሪያ

ሰኞ 24 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:28:55

ለዓመታት በጥርጣሬ እና በውጥረት ውስጥ የቆየው የሩሲያ እና የምዕራባውያኑ ግንኙነት ዩክሬን ውስጥ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ለይቶለት ወደ ግጭት እንዳይገባ ስጋት ከተፈጠረ ሦስት ዓመታት ሆኖታል። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ፊት ለፊት ከምታደርገው ጦር ባሻገር ከምዕራባውያን ጋር በሌላ ግንባር የአሻጥር ጦርነት እያደረገች ነው ሲል የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ማኅበር (ኔቶ) ያምናል። ለዚህም ሩሲያ ምሥጢራዊ ጥቃቶችን እየፈጸመች እና እየተዘጋጀች ነው በሚል ትከሰሳለች።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ ከሌሎች መሪዎች ለምን የተለየ ሆነ?

ማክሰኞ 4 ማርች 2025 ጥዋት 7:38:03

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሦስት ዓመታት በታላላቅ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሳይቀር በተለየ አለባበስ የሚቀርቡት የፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ አነጋጋሪ ሆኗል። ዋይት ሐውስ ውስጥ ለምን ሥልጣናቸውን የሚመጥን ልብስ እንደማይልበሱ እና ሙሉ ልብስ እንዳላቸው የተጠየቁት ዜሌንስኪ በኃይለ ቃል ምላሽ ሰጥተዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ እንደሌሎቹ የዓለም አገራት መሪዎች ለምድን ነው ሙሉ ልብስ የማይለብሱት?

አሜሪካ ከ15 ዓመታት በኋላ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው በአልሞ ተኳሾች የሚፈጸም የሞት ቅጣት

እሑድ 9 ማርች 2025 ጥዋት 4:59:01

በአሜሪካ ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ አንድ ሞት የተፈረደበት እስረኛ በአልሞ ተኳሾች በጥይት አርብ ዕለት ተገድሏል። የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብራድ ሲግሞን የተሰኘው ፍርደኛ የሞት ቅጣቱ በጥይት ተፈጻሚ እንዲሆንበት ብይኑን ረቡዕ ዕለት ነበር ያስተላለፈው።

ሞታቸውን ለማፋጠን የሚጾሙ ሃይማኖተኞች እንዳሉ ያውቃሉ?

ዓርብ 28 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 3:42:03

በዓለማችን ላይ ያሉ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጥንካሬ፣ ለአካላቸው ጤንነት እንዲሁም ከሞት በኋላ በሚኖረው ዓለም መልካም ነገሮችን ለማግኘት ይጾማሉ። በሕንድ ያሉት የጄይን እምነት ተከታዮች ግን በዕድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሞታቸውን ለማፋጠን አጥብቀው ይጾማሉ።

ሞባይላችን እንቅልፋችንን እያደናቀፈ መሆኑን ልብ ብለናል? ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል?

ሰኞ 17 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:01:22

ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል? ምን እናድርግ?

ኢንሱሊን መላመድ ምንድን ነው? በፆም ወቅትስ እክል ይፈጥራል?

ዓርብ 14 ማርች 2025 ጥዋት 4:00:54

በጡንቻ፣ በስብ እና በጉበት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ለኢንሱሊን መስጠት ያለባቸውን ምላሽ ሲያስተጓጉሉ ኢንሱሊን መላመድ ተፈጥሯል ማለት ነው። ከደም ውስጥ ጉሉኮስ ወስዶ ማከማቸት እንዲሳናቸው ያደርጋል።

በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒት

ረቡዕ 12 ማርች 2025 ጥዋት 4:12:46

በዩናይትድ ኪንግደም ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ችግር የገጠማቸው ሴቶች የተሰጣቸው መድኃኒት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተነገራቸው ለቢቢሲ ገለጹ። ሕክምና ከወሰዱ መካከል 20 ሴቶች ለቢቢሲ እንደገለጹት የተሰጣቸው መድኃኒት "አሉታዊ ወሲባዊ ባህሪ" እንዲያዳብሩ የሚያደርግ መሆኑ አልተነገራቸውም።

ኢሉሚናቲዎች መነሻቸው ከየት ነው? ዓለምንስ በምሥጢር 'ይቆጣጠራሉ'?

ሐሙስ 6 ማርች 2025 ጥዋት 3:55:36

"ኢሉሚናቲዎች በምሥጢር ዓለምን ተቆጣጥረው አዲስ ሥርዓት ሊዘረጉ ነው" የሚለው መላ ምት ለዓመታት ሲሰማ ቆይቷል። የዚህ ሃሳብ መነሻ በአውሮፓውያኑ 1960ዎቹ የነበረ ልብ ወለዳዊ ክስተት ነው። ጀርመን የነበረው 'ኢንላይትመንት ኢራ' ወይም የዕውቀት ብርሃን ዘመን ከኢሉሚናቲ መነሻ ጋር ይተሳሰራል።

በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው ይመከራል?

ሰኞ 3 ማርች 2025 ጥዋት 4:11:47

ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?

ወባን ለመሳሰሉ በፓራሳይት ለሚመጡ በሽታዎች ክትባት ማዘጋጀት ለምን ፈታኝ ሆነ?

ሰኞ 24 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:29:39

በታዳጊ አገራት ውስጥ በስፋት የሚሠራጩትን እና በርካቶችን ለሞት እና ለጉዳት የሚዳርጉትን ወባን የመሳሰሉ በፓራሳይት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ክትባቶችን ማግኘት አዳጋች ሆኖ ቆይቷል። በቅርቡ ለወባ መከላከያ የሚሆን ክትባት ከዓመታት ልፋት በኋላ ዕውን ሆኗል። ለመሆኑ ለእንዲህ ዓይነት በሽታዎች ክትባት ማግኘት ለምን ፈታኝ ሆነ?

የሚደክምዎ እና ሰውነትዎ ድንገት የሚዝል ከሆነ ኃይል ለማግኘት የሚረዱ 5 ቀላል መፍትሄዎች

ቅዳሜ 22 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:58:48

አንዳንድ ሰው ቶሎ ይደክመኛል ይላል። አንዳንድ ሰው “ምግብ ስበላ ራሱ ይደክመኛል” ይላል። አንዳንዱ ደግሞ ቀኑን ገና ሳያጋምሰው “እንቅልፍ-እንቅልፍ ይለኛል” ይላል። ያለምክንያት ይደምዎታል? ሰውነትዎ ድንገት ይዝላል? እነዚህን 5 ቀላል የምግብ ለውጦችን ይሞክሩ።

የእርጅና ምልክቶችን የሚያዘገየው እና በቆዳችን ጤንነት ላይ ጉልህ ውጤት የሚኖረው ምርምር

ዓርብ 21 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:06:16

ተመራማሪዎች የእርጅና ምልክቶችን ለማዘግየት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ የተባሉ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ይፋ አድርገዋል። የተመራማሪዎቹ ቡድን፣ የሰው አካል ከስቴም ሕዋስ እንዴት ቆዳን እንደሚፈጥር እንዲሁም የተወሰነ መጠን ያለው ቆዳን በቤተ ሙከራ ውስጥ ማምረት እንደሚቻል ደርሶበታል።

የምግብ ሸቀጦችን ትንሽም ቢሆን በጅምላ እና በችርቻሮ መሸመት ያለው ጥቅም ሲሰላ

ሰኞ 17 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:03:56

የምግብ ሸቀጦችን በጅምላ መግዛት ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው። አንደኛ ወጪ ይቆጥባል። ሁለተኛ ለአካባቢ ጥበቃ ያግዛል። ሉሲ በየጊዜው ደጋግሞ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ መግዛት አንድ ጊዜ ከመግዛት አንጻር ያለውን ልዩነት ካወቀች በኋላ ወርሃዊ ወጪዋን እንዳስተካከለች ትናገራለች።

ሞባይላችን እንቅልፋችንን እያደናቀፈ መሆኑን ልብ ብለናል? ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል?

ሰኞ 17 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:01:22

ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል? ምን እናድርግ?

በልምምድ የሚዳብረው በርካታ ፈዋሽ ጠቀሜታ ያለው የአተነፋፈስ ጥበብ

ቅዳሜ 15 ፌብሩዋሪ 2025 ጥዋት 4:51:13

የአተነፋፈሳችን ሁኔታ በጤናች ላይ የራሱ የሆነ ውጤት አለው። የተለያዩ የአተነፋፈስ ዘዴዎችን በመጠቀም በሰው ልጆች ጤና ላይ ለውጥ ማምጣት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የታወቀ ነው።

“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት

ሰኞ 18 ኖቬምበር 2024 ጥዋት 3:53:07

ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።

ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ

ሰኞ 30 ሴፕቴምበር 2024 ጥዋት 4:13:42

ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።

"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ

ሐሙስ 19 ዲሴምበር 2024 ጥዋት 4:54:19

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ

ዓርብ 24 ሜይ 2024 ጥዋት 4:16:17

ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።

ለአራት ዓመታት ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመኖር የተቀረጸው ፊልም፡ ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’

ሰኞ 16 ዲሴምበር 2024 ጥዋት 4:18:56

የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።

የሳንቲም ትዝታዎች - ፕሮፌሰር እሌኒ ዘለቀ ስትታወስ

ቅዳሜ 20 ጁላይ 2024 ጥዋት 4:33:56

“ሐኪሞቹ ‘ሰዓት አልቋል’ አሉ። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ይቺን ምድር እሰናበታለሁ።” እነዚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር እና የፖለቲካ ሳይንቲስት እሌኒ ሳንቲም ዘለቀ ቃላት ናቸው። ፕሮፌሰር እሌኒ ይህን መልዕክት በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ካስተላለፈች አንድ ሳምንት በኋላ ኒው ዮርክ በሚገኘው ኢስት ኢንድ ሆስፒስ ውስጥ ሕይወቷ አልፏል። ተማሪዎቿ፣ ወዳጆቿ እና የሚያውቋት እሌኒን እና ሥራዎቿን ዘክረዋል።

በቲክቶክ ዘመን ቆዳ አልፍተው፣ ብራና ወጥረው፣ ቀለም በጥብጠው ግዕዝ የሚማሩት የአዲስ አበባ ሕጻናት

ዓርብ 13 ሴፕቴምበር 2024 ጥዋት 4:01:27

አዳጊዎች ናቸው፤ የተገፈፈ የፍየል ቆዳ ያለፋሉ። ይደጉሳሉ። ይጠርዛሉ። ካራ፣ ጉጠት፣ መጥረቢያ. . . ተጠቅመው ቆዳ ያለሰልሳሉ። ቀጨም ተጠቅመው ብራና ይወጥራሉ። ይህን ሁሉ የሚሠሩቱ ርቆ ከሚገኝ መንደር ያሉ ቆሎ ተማሪዎች አይደሉም፤ ዘመናይ ከተሜዎች እንጂ። አንዳንዶቹ የቦሌ እና የካዛንቺስ ልጆች፤ አንዳንዶቹ የሳር ቤት እና የሲኤምሲ ተወላጆች ናቸው። ደግሞ ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ መሀል ፒያሳ ላይ ነው።

የኩላሊታችንን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ 6 ቀላል መንገዶች

ዓርብ 29 ማርች 2024 ጥዋት 4:06:46

በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋሉ ከሚታዩ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የኩላሊት ችግር አንዱ እየሆነ መጥቷል። ወሳኝ ከሆኑት የሰውነት ክፍሎች መካከል አንዱ የሆነው ኩላሊት በተለያዩ ምክንያቶች እክሎች ይገጥሙታል። ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር እና ጥንቃቄ በማድረግ ጤናማ ኩላሊት እንዲኖረን ማድረግ ይቻላል። ከእነዚህም መካከል ለኩላሊት ጤና የሚረዱ ስድስት ቀላል ጥንቃቄዎችን እነሆነ. . .

የላጤዎች ጉባኤ በቦሌ

ቅዳሜ 16 ኖቬምበር 2024 ጥዋት 4:43:38

በፈረንጅ አፍ ‘ስፒድ ዴቲንግ’ ይባላል። የአማርኛ አቻ የለውም። በአቋራጭ መተጫጨት ነው-ነገሩ። ፖለቲካዊ ቋንቋ ይመስልብናል እንጂ ‘የትዳር ማሳለጫ’ ሊባል ይችላል። ነገሩ ‘የፍቅር-ጉድኝት’ ለመፍጠር የሚደረግ አጭር ጉዞ ነው። የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት አደን እንደመውጣት ያለ ነው። የትዳር አሰሳ. . . የወደፊት ውሃ አጣጭን ለማማለል የሚሰጥ የአምስት ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ነው። የት? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ. . .

ምሥሎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዴት ይሠራሉ? ከእውነተኞቹስ እንዴት መለየት ይቻላል?

ማክሰኞ 19 ዲሴምበር 2023 ጥዋት 4:19:42

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) አማካይነት የሚዘጋጁት ምሥሎች ለእውነታ በእጅጉ የቀረቡ በመሆናቸው ምክንያት ትክክለኛ ፎቶዎች ወይም የሰው ልጅ የአእምሮ እና የእጅ ሥራ ውጤት ከሆኑት አንጻር ለመለየት አዳጋች እየሆኑ መጥተዋል። ታዲያ በዚህ ቴክኖሎጂ የተዘጋጁትን ምሥሎች ከእውነተኞቹ እንዴት መለየት እንችላለን?

የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?

ሐሙስ 29 ፌብሩዋሪ 2024 ጥዋት 4:14:38

ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?

እየፈረሰች ያለችውን አዲስ አበባ በመሰንቆ 'እየገነባት' ያለው ሀዲስ ዓለማየሁ

ቅዳሜ 11 ጃንዋሪ 2025 ጥዋት 4:35:47

ሀዲስ ዓለማየሁ መሰንቆ ተጫዋች ነው። ስለ መሰንቆ አውርቶ አይጠግብም። ዓለም ሙሉ በአንዱ የመሰንቆ ገመድ ቢተሳሰርለት ምኞቱ ነው። ሀዲስ እና መሰንቆን መለያየት አይቻልም ይላል። ስሙንና የሚወደውን መሰንቆ ገምዶ ራሱን ሀዲንቆ ሲል ይጠራል። የመጀመሪያን አልበሙን በቅርቡ ለቋል። አልበሙ እየፈረሱ ባሉት ቀደምት የአዲስ አበባ ሰፈሮች እና ጎዳናዎች ትዝታ የተሞላ ነው።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ብቅ ጥልቅ የሚሉት ግዙፎቹ “ባዕድ አብረቅራቂ ወጥ ብረቶች”

ሐሙስ 20 ጁን 2024 ጥዋት 4:08:35

ከቀናት በፊት በአሜሪካ የታየው ግዙፍ ባዕድ ነገር መነጋገሪያ ሆኗል። ነገር ግን ይህ ከስተት የመጀመሪያ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎቸ ውስጥ ታይተዋል። አመጣጣቸውም ሆነ ምንነታቸውም ለበርካታ መላ ምቶች ክፍት ሆኗል። የሌላ ዓለም ፍጡራን የተከሏቸው፣ የጥበብ ሥራዎች. . . ሌላም ሌላም እየተባሉ ነው። እስካሁን ምን የሚታወቅ ነገር አለ?